top of page






''ደብረ ታቦር'' (በሌላ ስሟ '' ሰማራ'' ) በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከጣና ሓይቅ ሰሜናዊ ምስራቅ 50 ኪሎ ሜተር ርቃ የምተገኝ በተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። በከተማይቱ ዙሪያ 48 ምንጮችመኖራቸው ለከተማይቱ እድገት ከፍትኛ አስተዋጾ ቢያደርጉም በ20ኛው ክፍለ ዘመን የባህር ዛፍ ተክል በከተማይቱ መሰራጨት ምንጮቹ እንዲደርቁ አድርጓል። የደብረታቦርን መሰረት የጣለው የ14ኛ ክፍለዘመን ንጉስ አጼ ሰይፈ አርድ(1344-1372) ነበር። በዚህ ንጉስ ዘመን ጥንታዊው የታቦር እየሱስቤ/ክርስቲያን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ታነጸ። ቤተ ክርስቲያኑ በንዲህ ከቆየ በኋላ በ18ኛ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በራስ ጉግሳ ሙርሳ እንደገና ታድሶ ተሰራ። ራስ ጉግሳ የደበረታቦር ከተማን በዚያው ስም ከሚታወቀው ተራራ ሰሜን ትይዩ እንደቆረቆረ ይነገራል።Ref - Jäger 1965 p 75 ራሱና ልጆቹ ለከተማይቱ መቋቋም አስተዋጾ ቢያበረክቱም ከተማይቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሰፊው የምትጠቀሰው አጼ ቴወድሮስ እና ከዚያም ቀጥሎ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በማገልገል ነው። ከሞላ ጎደል ደብረ ታቦር(ሳማራ) የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች። ደብረ ታቦር ካርታ|ተጭነው ስለተለያዩ የከተማይቱ ክፍሎች መርጃ የሚያገኙበት ካርታ እዚህ ይገኛል።
== ታሪክ ==
=== በ1300 ወቹ ===
አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) በደብረታቦር ተራራ (እየሱስ ተራራ) ላይ የእየሱስ ቤክርስቲያንን መሰረቱ Ref- Friedrich Heyer, Die Kirche in Dabra Tabor, Erlangen 1981 (Oikonomia 13)። ይህ ቤ/ክርስቲያን አሁን ድረስ ከዚያ ዘመን የመነጩ ቅርጻቅርጾች ሲኖሩት ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ራስ ጉግሳ ሙርሳ በቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ለውጥ አድርገዋል። ስለሆነም በቤ/ክርስቲያኑ የሚገኙ ስዕሎች ባብዛኛው ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ የሚመነጩ ናቸው። Ref - Éthiopie By Luigi Cantamessa, Marc Aubert ገጽ 181
=== በ1500 ወቹ ===
የደብረታቦር ስም በአጼ ልብነ ድንግል ዜና መዋዕል ላይ ሰፈረ።
=== በ1700 ወቹ ===
በ1700ወቹ መጨረሻ አካባቢ አሊ ጓንጉል (ትልቁ አሊ) የተባለ የየጁ ስርወ መንግስት መሪ በደብረ ታቦር አካባቢ ሃይለኛ መሪ በመሆን ከሱ በኋላ ለ80 ዓመታት ያክል የጸና ስርዓት በአካባቢው እንዳንሰራፋ ባህሩ ዘውዴ መዝግቧል Ref - ባህሩ ዘውዴ 1991 ገጽ 19 እንደ ታሪክ አጥኝው ሞርድካይ አብር አስተያየት የደብረታቦርን ከተማ የመሰረታት ይሄው ትልቁ አሊ ነበር። እንደ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስትግን ራስ ጉግሳ ሙርሳ ነበር።
=== በ1800 ወቹ ===
====1800 ====
በ1800 አካባቢ ራስ ጉግሳ ሙርሳ የተባለው የበጌምድር መሪ (1803-25) ደብረ ታቦርን እንደ ጦር ቅጥር በተራሮች መካከል መሰረተ። በትውፊት ሲነገር ራስ ጉግሳ ደብረታቦርን የመረጠበት ምክንያት አንድ መነኩሴ «ሴት አቦ ሸማኔ አድነህ በምትገልበት ቦታ ከተማህን አሰራ» ብሎ ስላዘዘው ነበር ይባላል። ሮቢንሰን የተባለ የታሪክ አጥኝ ስለ ራስ ጉግሳ ሲናገር «በዚህ በ19ኛ ክፍለ ዘመን አጥቢያ ላይ ራስ ጉግሳ ከሁሉ የኢትዮጵያ መሳፍንት ይልቅ የአገሪቱን አንድነት የበለጠ የሚወክል ነበር። በዚህ ምክንያት ከሞተም በኋላ ደብረታቦር የአገሪቱ የፖለቲካ ማዕከል እና መምሪያ ልትሆን በቃች»<ref>[Rubenson 1976 p 35]</ref> ራስ ጉግሳ 1825 ላይ ደብረታቦር ላይ ሲሞቱ እ.ኤ.አ ግንቦት 25፣ ሰኞ ዕለት እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቀብራቸው ሆነ። ዘመኑ በታሪክ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ለ27 ዓመት ራስ ጉግሳ የአገሪቱ እንደራሴ በመሆን አገልግለዋል። በእየሱስ ቤ/ክርስቲያን የርሱ ተከታይ መሪወች ኢማም፣ ማርየ እና ዶሪ የተባሉትና የዶሪ የአጎት ልጅ ራስ አሉላ አሊ (ትንሹ አሊ) እንዲሁ ተቀብረዋል። እንደ ታሪክ አጥኝው ማቲወስ ለኒህ መሪወች ማስታወሻ በጎንደር ግንብ ዘዴ የተሰራ የእንቁላል ግንብ በእየሱስ ቤ/ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ቆሟል። ከቤ/ክርስቲያኑ አጠገብም ቤ/መንግስቱ ይገኝ ነበር። አሊ አሉላ (አሊ ትንሹ) በቤተመንግስቱ የውጭ ቆንጽላወችን ያስተናግድ እንደንበርና እስካሁን ድረስ ለፍርድ እርሱ ይቀመጥበት የነበር የሚባል የድንጋይ ዙፋን በአካባቢው እንደሚገኝ ማቲወስ የተሰኘ የታሪክ አጥኝ ይገልጻል።
Ref -Äthiopien 1999 p 318 + Mathew 1947 p 154</ref> for more information
pleasevisit http://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ደብረ_ታቦር_%28ከተማ%29&action=edit



bottom of page